ኤርባስ A380 ሱፐርጃምቦ አውሮፕላን የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ ተጠቅሞ በረራ አደረገ 👇


ኤርባስ A380 ሱፐርጃምቦ አውሮፕላን የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ ተጠቅሞ በረራ አደረገ

ኤርባስ A380 ሱፐርጃምቦ አውሮፕላን የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ ተጠቅሞ በረራ አደረገ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በዓመት 200 ቢሊየን ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ ጥቅም ላይ ይውላል


አውሮፕላኑ በፈረንሳይ ቱሉዝ እና ኒስ ከተሞች መካከል የመጀመሪያ የ3 ሰዓት በረራ አድርጓል

የዓለማችን ግዙፉ አውሮፕላን “ኤርባስ A380 ሱፐርጁምቦ” የምግብ ማብሰያ ዘይትን እንደ ነዳጅ በመጠቀም የተሳካ የሶስት ሰዓት በረራ ማድረጉ ተገለፀ።

27 ቶን የምግብ ማብሰያ ዘይት (ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ) የተሞላው አውሮፕላኑ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ከፈረንሳይ ቱልዝ በመነሳት ኒስ ከተማ ማረፉ ተሰምቷል።


ኤርባስ A380 ሱፐርጁምቦ አውሮፕላን መቶ በመቶ የምግብ ማብሰያ ዘይት (ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ) በረራ ሲያደርግ የመጀመሪያ ነው የተባለ ሲሆን፤ ሌሎች የኤርባስ ስሪት አውሮፕላኖች ግን ባሳለፍነው ዓመት 3 የተሳካ በረራ አድርገዋል።

የካርበን ልቀትን በ80 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የምግብ ዘይት ነዳጅ፤ ጥቅም ላይ ከዋለ የምግብ ዘይት፣ ከስብ እንዲሁም ለምግብነት ከማይውሉ ሰብሎች የሚሰራ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ዘይቱ ካርቦን ከአየር ላይ መሰብሰብ በሚችልበት ሁኔታ ሰራሽ በሆነ መንገድ የሚመረት መሆኑም ነው የተገለፀው።

ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር (IATA) ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ የተባለው ዘይት የካርበን ልቀትን በመቀነስ ረገድ 65 በመቶ ሚና ይኖረዋል ብሏል።


በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በ2050 የካርበን ልቀትን በወ ዜሮ ለማምጣት የተያዘውን እቅድ ለማሳካት እንደሚረዳም ማህበሩ አስታውቋል።

እንደ ኤርባስ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ሁሉም አውሮፕላኖቹ እስከ 50 በመቶ የሚሆነውን ዘላቂነት ያለው የአቪዬሽን ነዳጅ ማለትም መደበኛውን ነዳጅ ከኬሮሲን ጋር ቀላቅለው ለመብረር የሚያስችላቸው የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።

በዓለም ደረጃ በዓመት 200 ቢሊየን ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ ጥቅም ላይ እንደሚውል መረጃዎች ያመለክታሉ።


እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

                   🦋SOT 🦋
            

Post a Comment

1 Comments

Hello, Dear friends, Welcome to 🦋 SOT 🦋 You can learn online and improve your skills