fixed wing (UAV) የድሮን

 



ሰላም ሰላም እስቲ ደሞ ዛሬ አዲስ የሰራውትን fixed wing (UAV) የድሮን አይነት ላስተዋውቃችሁ

(fixed wing(UAV)) ከተሳፋሪ አውሮፕላኖች ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ፣ ቋሚ ክንፍ ያለው ባለ አንድ ወይም ሁለት ሞተር የሚጠቀም ድሮን ነው ።
በረጅሙ ዘንበል ባሉ ክንፎቹ Aerodynamic ቅርፅ ተመርኩዞ የሚሰራ የድሮን አይነት ነው።

እንደ ባለብዙ ሞተር (ዲናሞ) ተጠቃሚ ድሮኖች በተቃራኒ ፣ እነዚህ ድሮኖች(UAV) ከፍ ብለው ለመቆየት ብዙ ባትሪ አያስፈልጋቸውም ምክንያቱም የሚጠቀሙት ሞተር አንድ ወይም ሁለት ነው።
ለምሳሌ አንድ ድሮን Quadcopter አራት ሞተሮችን ይጠቀማል ።
ስለዚህ መደበኛ ድሮኖች ለ አራት ሞተር የሚያወጡትን ሀይል ወደዚህኛው ስናመጣው ለአንድ ብቻ ይሆናል ።

የአሰራር ቅርፃቸው እና የሚሰሩበት ማቴሪያል ደግሞ ዋናው አየር ላይ ብዙ ሰአት የመቆየታቸው ምክንያት ነው

(fixed wing(UAV)) ድሮን ለመብረር የእጅ ማስነሳት ወይም መወርወር ያስፈልጋል ፣ እና ፓራሹት ይፈልጋሉ።
ለማረፍ ደሞ ለስላሳ መሬት ይፈልጋሉ ።

እነዚህን አይነት ድሮኖች ባደጉት ሀገራት ለስለላ ፣ ለመሬት ካርታ ስራና ለግብርና ስራ አገልግሎት ላይ ውለዋል ።

ከኔጋር አብሮ መስራት የሚፈልግ ወይም በሀሳብ እና በማቴሪያል ሊደግፈኝ የሚፈልግ ሰው ካለ 🦋 SOT🦋ላይ አናግሩኝ ።

#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

               🦋SOT 🦋
              

Post a Comment

0 Comments