አዲስ አውሮፕላኖች ወደ ገዥዎቻቸው እንዴት ይጓጓዛሉ❓🤔

 አዲስ አውሮፕላኖች ወደ ገዥዎቻቸው እንዴት ይጓጓዛሉ❓🤔


አዳዲስ አውሮፕላኖች ወደ ገዥዎቻቸው የሚጓጓዙበት መንገድ አውሮፕላኖቹ✈️ በአንድ ጊዜ በረራ እንደሚሸፍኑት ርቀት ይወሰናል፡፡

ለምሳሌ፣ አነስተኛ አውሮፕላኖች በአንድ ጊዜ በረራ ገዢዎቻቸው ጋር መድረስ ስለማይቸሉ በጉዟቸው መስመር ውስጥ የሚገኙ ቅርብ ቅርብ አካባቢዎች እየፈለጉ በማረፍ ነዳጅ እየሞሉ ዳግም መብረር ግድ ይላቸዋል፡፡

ከሰሜን አሜሪከ ተነስቶ መዳረሻውን ሲድኒ አውስትራሊያ ማድረግ የፈለገ አዲስ አነስተኛ አውሮፕላን በርካታ አውሮፕላን ማረፊያዎች እያረፈ ነዳጅ መሙላት አለበት፡፡ ይህም ማለት ጃፓን፣ ቻይና እና ኢንዶኔዢያ ደርሶ ከማረፉ በፊት ቅድሚያ ከዋሽንግተን ተነስቶ አላስካ ላይ አርፎ የነዳጅ ማጠራቀሚያውን ሙሉ ማድረግ ያስፈልገዋል፡፡ በመጨረሻም ሲድኒ ከመድረሱ በፊት ኢንዶኔዢያ ዳርዊን አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን ይረግጣል፡፡

ታዲያ ምንም እንኳን እያንዳንዱ በረራ እስከ 3218 ኪ.ሜ እንደሚሸፍን ቢታወቅም አውሮፕላኑ ግን በአንድ ጊዜ መሉ ነዳጅ ብቻ ይሄን ያክል ኪ.ሜ መብረር ስለማይችል በአብዛኛው ተጨማሪ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ይገጠምለታል፡፡


አዲስ የመንገደኞች አውሮፕላኖችም ከዚህ ጋር ተመሳሳይነት ባለው መንገድ ነው ወደ ገዥዎቻቸው የሚደርሱት፡፡ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን 9000 ማይልና ከዚያ በላይ ርቀት በአንድ ጊዜ መብረር ይችላል፡፡ እንግዲህ ገዥው ከአምራቹ ኩባንያ በዚህ የርቀት ክልል ውስጥ የሚገኘ ከሆነ አውሮፕላኑን ቀጥታ በማብረር እንዲረከብ ይደረጋል፡፡

ከዚህ ክልል ውጭ ከሆነ ደግሞ አውሮፕላኑ ተጨማሪ ርቀቶችን መሸፈን የሚያስችለው ነዳጅ የሚይዝበት ተጨማሪ የነዳጅ ሰልባትዮ የእቃ መጫኛው ውስጥ አልያም የመንገደኞች መቀመጫ የሚገኝበት ቦታ ላይ ይገጠምለታል፡፡

እንግዲህ የመንገደኞች አውሮፕላኖች ዋና ዋና አምራቾች ኤርባስ እና ቦይንግ ብቻ ናቸው፡፡ ከሁለቱ አምራቾች መካከል የቦይንግ አውሮፕላኖች የሚመረቱት በሰሜን አሜሪካ ስለሆነ ብዙ ርቀት መጓዝ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

ለምሳሌ ቦይንግ 747-8፣ 777-200LR እና 787-9 የሚመረቱት ዋሽንግተንና ካሊፎርኒያ ውስጥ በሚገኙ የማምረቻ ተቋማት ውስጥ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከአውሮፕላኖቹ የበረራ ርቀት ውጭ የሆኑ ገዥዎች ጋር አውሮፕላኑ እንዲደርስ የግድ ተጨማሪ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ሊገጠምለት ግድ ይላል፡፡

ኤርባስ ግን ከቦይንግ ለየት ይላል፡፡ ኤርባስ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ስፔን እና ቻይና ውስጥ የአውሮፕላን መገጣጠሚያ ተቋማት ስላሉት ብዙ ጊዜ አውሮፕላኖቹን የመገጣጠም የመጨረሻ ሂደት የሚከናወነው በገዥዎቻቸው ክልል ውስጥ ስለሆነ በርክክብ ጊዜ ግማሽ አለምን ለመዞር ትርፍ የነዳጅ ማጠራቀሚያ መግጠም ግድ አይለውም፡፡

                   🦋#SOT🦋


Post a Comment

0 Comments