ሰውኛ ሮቦቶች /humanoid robots/

 

📌ሰውኛ ሮቦቶች /humanoid robots/

ሰው ሰራሽ ክህሎት እና የሮቦቲክ አሰራር የተገጠመላቸው ቴክኖሎጂዎች በጦርነት ዘርፍ ከገቡ ከራርመዋል፡፡ ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው የድሮን ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ፓይለቱ በሺህ ኪሎሜትሮች ርቆ ድሮኑን በሪሞት ኮንትሮል በመቆጣጠር የሚፈለገውን ኢላማ መቶ የጠላትን ግዛት መደምሰስና ሰውን መግደል ይችላል፡፡ የወደፊቱ ስጋት ደግሞ ከዚህ ባለፈ መልኩ የሮቦት ወታደሮች ቢፈጥሩስ የሚል ነው፡፡

እንደዚህ ያለው ፈጠራ ህያው ከሆነ የጦርነት መልክ ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ እስከ ወዲያኛው ሊቀየር ይችላል፡፡ አቅም የሌላቸው ሀገራት የሰው ወታደር ሲያሰልፉ ኃያላኑ በሮቦት ወታደሮቻቸው የሚዋጓቸው ከሆነ ጦርነት አዲስና አስፈሪ መልክ ይይዛል ማለት ነው፡፡

ጦርነት መቼም ቢሆን በጎ ገጽታ ኖሮት አያውቅም፣ ወደፊትም አይኖረውም! ይሁንና መከሰቱ በማይቀር ወቅት ግን ይብዛም ይነስም ዓለም ዓቀፍ መተዳደሪያና ደንብ አለው፡፡ እንደ ኒኩሊየር ቦንብ ያለ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አልያም ደግሞ የኬሚካልና ባዮሎጂካል መሳሪያን በጦርነት ላይ መጠቀም አይቻልም የሚል ስምምነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተተግብሮ የሚገኘውም በዚህ ምክንያት መነሾ ነው፡፡

ኤሎን መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ገዳይ ሮቦቶች ፈጽሞ እንዳይሰሩ ካሁኑ ጠንካራ እገዳ መጣል አለበት ሲሉ የተባበሩት መንግስታት ይህን ጉዳይ በህግ ደረጃ እንዲያስፈጽም ዋና ኃላፊነትን ወስዶ መስራት አለበት ብለዋል፡፡

በርግጥ የስራ አጥነት ስጋት “ከእኛ ብቃት አልፈው እና ትዕዛዝ መቀበል አቁመው ይቆጣጠሩን ይሆን?” የሚል ፍርሃትና ሌሎች በርካታ የጎንዮሽ ስጋቶች እንዳሉ ሆነው የሮቦቶች በጎ ገጽታ ደግሞ የሚካድ አደለም፡፡

“እኛው የፈጠርናቸው ሮቦቶች ይገዙን ይሆን?” ተብሎ በሚሰጋበት ወቅትም የሰው ልጅ አዲስ ነገርን የማወቅ ጉጉቱ ከምድር አልፎ ህዋ ድረስ በመሄድ ጭራሽ አይቶ የማያውቀውን የአጽናፈ ዓለም ክፍል የማየት ፍላጎቱን ፈጽሞ አላቋረጠም፡፡

ምናልባትም የሰው ልጅ ወደፊት ለምርምር ብቻ ሳይሆን ለቱሪዝም እና ለጫጉላ ሽርሽር ከውብ ደሴቶች ባለፈ ጉዞውን ወደ ጠፈር ያደርግ ይሆን?
ማን ያውቃል ጊዜ ግን መልስ አለው!

                   🦋#SOT🦋

Post a Comment

0 Comments