Biometric Technology

 đŸ˜Žá‰Łá‹Žáˆœá‰ľáˆŞáŠ­áˆľ ቴክኖሎጂ


ባዮሜትሪክስ የሚለው ቃሉ ቀጥታ ከግሪክ የተወሰደ ሲሆን “ባዮ” ማለት ህይወት፣ “ሜትሪክስ” ደግሞ መለካት ወይም ልኬት ማለት ነው። ሁለቱ ቃላት በአንድነት ሲነበቡ ደግሞ የህይወት መለኪያ/ልኬት የሚለውን ትርጉም ይሰጣሉ። ባዮሜትሪክስ የአንድን ነገር ተፈጥሯዊ ባህሪ ማለትም የዲ ኤን ኤ አደራደር፣ የዓይን ቀለምና ምጣኔ፣ የእጅ አሻራ፣ የድምፅ ሞገድ፣ የልብና ነርቭ መንገድ እንቅስቃሴ የሚያጠና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው። ወይም ደግሞ ባዮሜትሪክስ የአንድን ሰው ማንነት በግልጥ በሰውነት ገፅታው ወይም በውስጣዊ ሥነ ህይወታዊ ባህሪው መረጃ ላይ በመመስረት ሾለ ሰውየው አጠቃላይ ሁኔታ ማውራት የሚያስችል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ነው።

እነዚህ ባህሪያት በቀላሉ #የማይረሱ፤ የማይጋሩና የማይሰረቁ መሆናቸው ልዩ የሚያደርገው ጉዳይ ነው፡፡

የባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ በጥንት ጊዜ ከክስቶስ ልደት በፊት ከ500BC ጀምሮ የባቢሎናውያን የንግድ ልውውጦች የጣት አሻራዎችን ሸክላ ላይ በማስቀመጥ ይጠቀሙ የነበረ ቢሆንም በትክክል በዘማናዊ ቴክኖሎጂ መልክ ይዞ ግን በስፋትና በረቀቀ መልኩ አገልግሎት መስጠት የተጀመረው እኤአ ከ1981 በኋላ ስለመሆኑ ይነገራል፡፡

በዚህም መሰረት ባዮሜትሪክስ ቴክኖሎጂ አሁን ካለንበት የቴክኖሎጂ ጣሪያ ላይ ደርሶ የረቀቁ ወንጀሎች ሲፈፀሙ የሰዎችን ማንነት ለማወቅ የሚጠቅም የአሻራ ቴክኖሎጂ በመሆን በስፋት አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ #ባዮሜትሪክስ ትልቅ ፋይዳ ያለው የቴክኖሎጂ ውጤት ሲሆን፤ አስፈላጊነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን የዓለም የደህንነት ጥያቄ በመመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

በተለይም በትምህርት ተቋማት፣ ህክምና ተቋማት፣ በታላላቅ ኢንዱስትሪዎች፣ መንግስታዊ በሆኑና ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በደህንነት ተቋማት እና በሌሎችም ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።

📍የባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂዎች መገለጫዎች:

ዩኒቨርሳሊቲ

በአለም ላይ ያለ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪ ሊኖረው ይገባል

ልዩነት

በአጠቃላይ ሁለት ሰዎች አንድ ዓይነት ባሕርይ የላቸውም፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ የሆኑ መንትዮች ለመለየት ከባድ ናቸው፡፡

ዘላቂነት

የሰዎች የባዮሜትሪክስ ባህሪ ከጊዜ ጋር ልዩነት ሊኖራቸው አይገባም፡፡ ለምሳሌ፣ የአንድ ሰው ፊት ከእድሜ ጋር ሊለወጥ ቢችልም በቴክኖሎጂው የመለየት እድሉ ሰፊ ነው።

ተቀባይነት

በሁሉም አለማት ላይ ተመሳሳይ መሆኑና ሁሉም የተቀበሉት መሆኑ

አስቸጋሪነት

ይህም ማለት ሰዎች ለመሸወድ ወይም ለማጭበርብር የማይሞክሩት መሆኑ

📍ባዮሜትሪክ ቴክኖሎጂ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች:

🔺 የጣት አሻራ ቴክኖሎጂ
🔺 የፊት ገፅታን የሚለይ ቴክኖሎጂ
🔺 የአይን እይታ ቴክኖሎጂ
🔺 የድምፅ ቴክኖሎጂ የሚሉት ከብዙዎች መካከል ጥቂቶች ናቸው፡፡

📍የባዮሜትሪክስ ጠቀሜታ

✅ የወንጀል ድርጊት ከመፈፀሙ በፊትና ከተፈፀመ በኋላ የሰዎችን ማንነት ለመለየት የሚያገለግል ቴክኖሎጂ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ሰው የተለያዩ አለማትን በሚዞርበት ወይም በሚጎበኝበት ወቅት በሚዳረስባቸው ቦታዎች በሚገኙ የኢሚግሬሽን ጣቢያዎች ላይ የጣት አሻራ እንዲሰጥ ይጠየቃል ይህም በሀገር እና ግለሰብ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ወይም የወንጀል ድርጊቶችን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡

✅ በበርካታ የመንግስትና የግል ድርጅቶች፣ ባንኮች እና የገንዘብ ተቋማት እንደ ሰዓት መቆጣጠሪያ ይጠቅማል፡፡

✅ የባዮሜትሪክ ሥርዓቶች ሰዎችን በፍጥነት፣ በቋሚነት እና በአስተማማኝ ሁኔታ በመለየት ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡

                   🦋#SOT🦋



Post a Comment

0 Comments