Four Forces of Flight በአውሮፕላን በረራ ወቅት ከመነሻው እስከ መድረሻው ይሚከሰቱ የአራቱ ኃይሎች ህግና አስገራሚ አሰራር👇👇

 

🛫🛬🛫🛬🛫✈️🛬🛫🛬🛫🛬

🛩 መኪና ውስጥ ስንሆን ከመሬት ወይም መኪናው ከሚሄድበት መንገድ  ያለንበት ከፍት በግምት ከ 50 cm እስከ 4 ሜትር ሊሆን ይችላል።

🛩  ይህም ከሞተር ሳይክል ጀምሮ እስከ ሁልት ደረጃ እስካለው ባስ ሊሆን ይችላል። በዚህም መኪናው ወደፊት ለምሄድ እንጂ ከመሬት ለመነሳት የሚታገልበት ምክንያት የለውም በራሪ መኪና ካልሆነ በስተቀር።

🛩  አውሮፕላን ሲሆን ግን መነሻውን መሬት አድርጎ መንገዱን ደግሞ  በአማካኝ ከመሬት ጠለል በላይ 35,000 ጫማ ወይም 10,668 ሜትር ከፍታ ላይ ነው።

🛩 ታድያ ከመሬት ላይ ተነስቶ ይህንን ከፍታ ደርሶ መንገድ ጨርሶ ወደታች ለመውረድ በጥንቃቄ የሚመራና ሳይንሳዊ የሆነ ህግን ተከትሎ በሰላም  መነሳትን፣ መብረርንና ማረፍን ተግባራዊ ያደርጋል።

🛩  በዚህ ሂደት ውስጥ አራት መሰረታዊ ሃይሎችን አንዱን ካንዱ ማመጣጠን ያስፈልጋል።

🛩 ለመነሳት በአውሮፕላኑ ክንፍና ባጠቅላይ በአውሮፕላኑ ቅርጽ  አማካኝነት መሚመነጨውን ሊፍት ሃይል (የመንሳፈፍ ችሎታ) ወደታች ከሚስበው ከመሬት ስበት ጋር ማመጣጠን አለበት። ለመነሳትም የግዴታ ሊፍት ከ መሬት ስበት መብለጥ አለበት።

🛩 በተጨማሪም በአውሮፕላኑ ሞተር ወደፊት የሚጎትተው ሃይል ወይም ትረስት ፎርስ የግዴታ አውሮፕላኑን ወደኋላ ከሚጎትተው የድራግ ሃይል መብለጥ አለበት።

🛩 በዚህም መሰረት አውሮፕላኑ በሚነሳበት ጊዜ (During Take off)  ሊፍት ከግራቪቲ፤ ትረስት ደግሞ ከድራግ መብለጥ አለበት ይህም የአውሮፕላኑ እሚፈልገው ከፍታ እስከሚደርስ ድረስ ተግባራዊ ይሆናል።

🛩 አውሮፕላኑ ከፍታ ላይ ከደረሰ በኋላ ሊፍት እና ግራቪቲ እኩል ይሆናሉ። ይህም በአውሮፕላኑ የሚመነጨው የመንሳፈፍና ከመሬት ስበት ጋር  በተቃራኒ አቅጣጫ እኩል ይሆናል።  በዚህ ላይ እንዳለ በተመሳሳይ ጊዜ በአውሮላን ሞተር የሚመነጨውና አውሮፕላኑን ወደፊት እንዲሄድ የሚያደርገው የትረስት ሃይል አውሮፕላኑን   ወዳ ከሚጎትተው የድራግ ሃይል መብለጥ አለበት። ይህም አውሮፕላኑን ያለችግር ወደፊት እንዲገሰግስና በአውሮፕላኑ ውስጥ ሰወች በቀላሉ እንዲንቀሳቀሱ ያስችላል።

🛩 ትልቁና ትኩረት የሚሰጠው ደግሞ (Landing) ማረፍ ነው።  በዚህ ጊዜ አውሮፕላኑ ከፊት ለፊት ከአፍንጫው ዝቅ በማለት የነበረውን ፍጥነት መቀነስና ያለውን የመንሳፈፍ አቅም መቀነስ ይጀመራል ። በዚህ ጊዜ  ግራቪቲ ከሊፍት ድራግ ደግሞ ከትረስት ይበልጣል። ይህ ሂደት በጥንቃቄና ቀስ በቀስ  የሚደረግ  ነው።

🛩 ነገር ግን አውሮፕላኑ በጣም ወደመሬት ሲጠጋ በፊት ሲበር ከነበረበት የመንሳፈፍ መጠን (ሊፍት) በጣም ይጨምራል።  ይህም አውሮፕላኑ ምንም እንኳን ክብደት ቢኖረውም  በፍጥነት ከመሬት ጋር እንዳይጋጭና ቀስ ብሎ እንዲያርፍ ያግዘዋል።  በዚህም የመሬትን ስበትን ለመቋቋም ሊፍትን በመጨመርና  ትረስት ሃይልን በመቀነስ ያመጣጥናል።

🛬አውሮፕላኑ መሬት ከነካበት ጊዜ ጀምሮ ደግሞ ድራግን እጂግ በጣም በመጨመርና ሊፍቱን ወይም የመንሳፈፍ አቅሙን በጣም በመቀነስ  አውሮፕላኑ በአጭር እርቀት ቶሎ እንዲቆም ለማድረግ ያግዛል።
                       🦋 SOT🦋
✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️✈️

#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

              
        

Post a Comment

0 Comments