በቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰሩት ሮቦት ውሾች

 

በቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ የተሰሩት ሮቦት ውሾች
******************
በጣም ፈጣን የሆነና ትእዛዝ አክባሪ የሮቦት ውሻ በቻይና መሰራቱ ተሰምቷል፡፡ ይህ አልፋ ዶግ

AlphaDog

የተሰኘው ሮቦት ውሻ የቻይናን በቤት እንስሳትና በቴክኖሎጂ ላይ ያላትን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሎለታል፡፡ ውሻው ከፍተኛ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) የታገዘ አካባቢውን ማየትና መስማት የሚያችል ብቃት ያለው ሲሆን ውደ ውጭ ይዘውት ወጥተው አብረውት ሊንቀሳቀሱ የሚችሉት ነው፡፡
ሮቦቱን ያመረተው ድርጅት ዌይላን የቴክኖሎጂ ሙያተኛ የሆኑት ማ ጄይ ሮቦቶ ከተፈጥሯዊው ውሻ ጋር ብዙ የሚያመሳስለው ነገር እንዳለ ተናግረዋል፡፡ የፈጠራ ባለቤቶቹ የሰሩት ሮቦት በሰዓት 15 ኪሎሜትሮች ያክል መጓዝ የሚችል እንደሆነና በዘርፉ ገበያ ላይ ካሉት በጣም ፈጣኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከብረት የተሰሩት አራቱ እግሮቹ ከተፈጥሯዊው ውሻ የተሸለ የተረጋጋ አካሄድ እንዲኖረው አድርጎታል ብለው እንደሚያስቡ የመረጃ ምንጫችን አስነብቧል፡፡
ሮቦቱ በራሱ መንቀሳቀስ እንዲችል ፈጣን የሆነ የአምስተኛ ትውልድ ኔትወርክን የፈጠራ ባለቤቶቹ የተጠቀሙ ሲሆን የ5G ቴክኖሎጂን መጠቀማቸው ችግር በሚገጥመው ጊዜ አፋጣኝ መልስ መስጠት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡ በመጀመሪያው የሽያጭ ወር 1800 ሮቦቶች የተሸጡ ሲሆን ዋጋቸውም 2400 የአሜሪካን ዶላር ወይም 16 ሺህ የቻይና ገንዘብ ነው፡፡ እንደ ሽያጭ ድርጅቱ መረጃ ከሆነ አብዛኛው ትእዛዝ የሚመጣው ከኮምፒውተር አበልጻጊዎች፣ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚሰሩና ምርቱን ይወዱታል ተብለው ከተጠበቁት ከህጻናት ነው፡፡
                   🦋 SOT🦋
#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ
               ●◉❖◉●

               
       

Post a Comment

0 Comments