የጂኒየስነት ሚስጥር .....!

 የጂኒየስነት ሚስጥር .....!



ክፍል » 5


📚 ከራሴ ልምድ በመነሳት ስለ አጠናን ዘዴዎች አንዳንድ ነገሮችን ላንሳላችሁ ፦

💭 በመጀመሪያ ስታጠኑ በተቻላችሁ መጠን ላለመጨናነቅ ሞክሩ። ስለ ውጤት መውረድ ወይም ስለትምህርቱ ክብደት እያሰባችሁ በጭራሽ ለማጥናት አትሞክሩ ምክንያቱም ምንም ትርፍ የለውም። ራሳችሁን ዘና አድርጉ motivated ሆናችሁ አጥኑ እመነኝ ትኩረት እስከሰጣችሁት ድረስ የማይሳካ ምንም ነገር የለም። አመናችሁኝ ❓ እንቀጥል ..!


💭 የተወሰኑ እኔን የጠቀሙኝን የጥናት ዘዴዎች ልንገራች ፤ ተከተሉኝ ፦



📍 ጥያቄ አውጡ ❓

📚 እስካሁን ከብዙ ሰዎች እንደሰማችሁት ጥያቄዎችን መስራት ውጤታማ የሆነ የጥናት ዘዴ ነው። የ worksheet , አጋዥ መፅሐፍት ፣ እንዲሁም text book  ጥያቄ መስራት ጠቃሚ እንደሆነ ታውቃላችሁ ብዬ አስባለሁ። ዛሬ እኔ ሌላ ቴክኒክ ላሳያችሁ....ምን በሉኛ ❓    በራሳችሁ ጥያቄ አውጡ።

📚 እኔ አስተማሪ ብሆን ኖሮ ምን ጥያቄ ነበር ልጆቼን የምፈትናቸው ብላችሁ አስቡ። ይሄንኑ ጥያቄ ራሳችሁን መልሳችሁ ፈትኑ። ከጓደኞቻችሁ ጋር ስሩት ። ለምን ይጠቅማል ያላችሁ እንደሆነ ከማንበብ በተጨማሪ የጥያቄ አወጣጥ (exam question concept) ታገኙበታላችሁ ።

ላውጋችሁማ ❓

📚 እኔ የማልረሳው አንድ ታሪክ አለ። የ elementary ተማሪ እያለሁ ሳይንስ አስተማሪያችን ፈተና ሲቃረብ አካባቢ አሳይመንት ሰጠን። አሳይመንቱ እኛ በራሳችን ጥያቄ አውጥተን ከነመልሱ ሰርተን ማስገባት ነው።  የሚገርመው ነገር እኔ ያወጣሁአቸውን ጥያቄዎች ፋይናል ፈተና ላይ በብዛት አገኘሁአቸው። የመምህራንን exam question psychology ስታገኙ ትምህርቱ ልክ እንደ ውሀ ቀላል ነው ሚሆንላችሁ።

    📍concept ያዙ ❓


📚 በጣም ብዙ ተማሪዎች በደንብ እያጠኑ ግን ውጤታማ ሳይሆኑ ሲቀሩ ይታያል።
ለምን ❓ ከተባለ የሚያነቡት መፅሐፉ ላይ ያለውን ፅሁፍ እንጂ Conceptun አይደለም። የምናነበው ነገር ስለምንድነው  እያወራ ያለው ❓ ምን እንድንይዝ ነው የተፈለገው ❓ ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።



✏️ ቆይ ጥናታችን ውጤታማ እንዲሆን ምን እናድርግ ❓


💡 ክላስ አትቅጣ

📚 ይብዛም ይነስም teacherሩ የሚነግረን concept ዋጋ አላት። ጂኒየስም ይሁን አይሁን የሚያስረዳበት መንገድ ይጣፍጥም አይጣፍጥ ክላስ ተከሰት ።


💡 ከጓደኞቻችሁ ጋር ተጠያየቁ። 

📚 አሪፍ ጀማ ሰርታችሁ ጥያቄ ፍለጡ ፤ ጥሩ እና መልካም ጓደኞች ጋር የሚደረግ ጥረት ትልቅ effect አለው ።

💡 informal way ተጠቀሙ።

📚 በጨዋታ (በቀልድ) አስታካችሁ የያዛችሁትን ዕውቀት ልትረሱ ብትፈልጉ ራሱ አትችሉም ፣ በፌዝ መልክ አውሩት።



እንደ ጉርሻ ❓

📚 ከformal ጥናት ውጪ በሆናችሁ ጊዜ በማያጨናንቃችሁ መልኩ meditate አድርጉት ። ተመስዕጦ ራስን ለማግኘት ምርጥዬ መንገድ ነው ። (የግል ምክር )

🔎 በተለየ መልኩ ደግሞ 💭


📍 አልችልም የሚል ሀሳብን አስወግዱ። ትችላላችሁ ...! መቻልን ተሸክሞ የመጣ የለም ሁሉም በምድር በጥረቱ አበጅቶት ነው ። 

📍 በሚመቻችሁ ጊዜና ቦታ አጥኑ። ቀን or ማታ  ላይብረሪ ወይም ከሰው ጋር  ብቻ እናንተ በለመዳችሁት setting ( የምታውቁትን ጎበዝ ተማሪ ሳይሆን የራሳችሁን መንገድ ፍጠሩ ..!)


📍ፈታ በሉ ፤ ግን ከትምሮ መቼም አትራቁ። because ርቆ መመለስ ከባድ ነው ሚያረግባችሁ ...ስትኖሩ ተማሪ መሆናችሁን አትርሱ ...!

💬ክፍል » 6 ይቀጥላል.........
           🦋SOT 🦋
🎲 JOIN AND SHARE
         

Post a Comment

0 Comments