የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንዴት ይሰራል⁉️

 የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንዴት ይሰራል⁉️


የዩኒቨርሲቲ ምደባ የሚሰራው እንደድሮው ጊዜ በቀጥታ በሰዎች ሳይሆን ዘመናዊ እና አለምአቀፋዊ ተቀባይነት ባለው ማሽን ነው።

ታድያምደባው ሲካሄድ በዋነኝነት የተማሪዎችን ውጤት መሰረት በማድረግ ነው፡፡ ይኸውም:-

ምደባው በቅድሚያ ምደባውን ለሚያከናውነው ማሽን እነዚህ የመረጃ ግብዓቶች inpute ይሰጡታል። እነሱም

👉 ከመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ  ተማሪዎች ስም ዝርዝር

👉 የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅም

👉 የመቁረጫ ነጥብ

👉 የተማሪዎች ውጤት

👉 PHASE (ምድብ)

PHASE  ማለት ለምሳሌ እነሱ inpute ሲያስገቡ

PHASE 1 ከ አንደኛ ምርጫ እስከ አምስተኛ ምርጫ

PHASE 2 ከ አምስተኛ ምርጫ እስከ አስረኛ ምርጫ ወ.ዘ.ተ እያለ እንዲሰጥ አድርገው program ያደርጉታል ማለት ነው።

ከላይ ያሉት የመረጃ ግብዓቶች ከገቡለት በኋላ ማሽኑ

1⃣ የተማሪውን ውጤት (ነጥብ)

2⃣ የተማሪውን የምደባ ምርጫ አሞላል

3⃣ የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን

መሰረት በማድረግ ተማሪዎችን ይመድባል፡፡ በዚህ መልኩ ምደባ ሲሰራ እነሱ ብቻ በሚያውቁት scale መሰረት:

➖ በጣም ጥሩ ውጤት ያመጣ ተማሪ
PHASE = ONE , CHOICE = ONE
ይደርሰዋል ማለት ነው። ማለትም የመጀመሪያ ምድብ የመጀመሪያ ምርጫ ማለት ነው፡፡

➖ ከዚያ scale ቀጥሎ ያመጣ ተማሪ ደግሞ: 
PHASE = 1 , CHOICE = 2
ይደርሰዋል ማለት ነው። ማለትም የመጀመሪያ ምድብ ሁለተኛ ምርጫ ማለት ነው።

የምደባ ውጤት በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል

#SHARE #Share #Share
━━━━━━━━ ● ━━━━━━━━
  ❇️𝐒𝐭𝐫𝐢𝐯𝐢𝐧𝐠 F𝐨𝐫 𝐄𝐱𝐜𝐞𝐥𝐥𝐞𝐧𝐜𝐞!
━━━━━━━━ ● ━━━━━━━━
               🦋SOT 🦋
━━━━━━━━ ● ━━━━━━━━
              

Post a Comment

0 Comments