ሜታ ኩባንያ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ ሰጥተዋል በሚል የቀረበበት ክስ አመነ

 

ሜታ ኩባንያ የተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ ሰጥተዋል በሚል የቀረበበት ክስ አመነ።

ሜታ ኩባንያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን የግል መረጃ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ ሰጥቷል በሚል የተወሰኑ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ለመሰረቱበት ክስ የ725 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱን የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ፌስቡክ የግል መረጃዎችን የሰጠው፣ "ካምብሪጅ አናላቲካ" ለተባለ ኩባንያ እንደነበር ተገልጧል።
"ካምብሪጅ አናላቲካ" ቀደም ሲል በኬንያና አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫዎች በመራጮች ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ተቀጥሮ ስለመስራቱ ሪፖርቶች መውጣታቸው ይታወሳል። ፌስቡክ በኢትዮጵያ "ጥላቻን በማሰራጨት" ወንጀል በቅርቡ ናይሮቢ ውስጥ በሁለት ኢትዮጵያዊያን ክስ እንደተመሠረተበት ይታወሳል።

            🦋SOT🦋

Post a Comment

0 Comments