ሊዮናርዶ_ዳቪንቺ

 

#ሊዮናርዶ_ዳቪንቺ

ከ1452-1519 ዓ.ም ድረስ የኖረው ✍#ሰዓሊ 🕵#የፈጠራ_ባለሞያ👱#መሃንዲስ👓#ፈላስፋ #የሂሳብ_ሊቅ #ሳይንቲስት📝#ፀሀፊ የሚሉት ስሞች ይህንን አስደናቂ #ጣልያናዊ ባለራዕይ ምሁር ሊገልፁት ይችላሉ::በብዛት የሚታወቀው የጌታ እራት "#The_Last_Supper" እና #ሞናሊዛ በተሰኙት አስደናቂ🖍ስዕሎች ቢሆንም እጅግ በርካታ ዘመን #ተሻጋሪ የሆኑ ድንቅ የፈጠራ🖌ዲዛይኖቹ ይህንን ታላቅ ምሁር ከስልጣኔ ፈር #ቀዳጅ👱አባቶች ተርታ ቅድሚያ ተሰላፊ አድርገውታል ቢባል #ማጋነን አይሆንም::

🔰ይህ ባለራዕይ ገና ሳይንስና #ቴክኖሎጂ በቅጡ እንኳን ትርጉም ሳይሰጠው የሰው ልጅ ወደፊት ከብዙ #መቶ አመታት በኃላ ይፈጥሯቸዋል ብሎ ያሰባቸውን ነገሮች👁‍🗨አስደናቂ በሆነ #ምናባዊ የፈጠራ ክህሎቱ🗒በወረቀት ላይ #አስፍሮ ነበር::
📦ሊዮናርዶ ዳ ቪንቺ #በተግባራዊ ደረጃ የፈጠራቸው ተጨባጭ ቁሶች #ባይኖሩም ዘመን ተሻጋሪ በሆኑ #የዲዛይን ስራዎቹና ከዲዛይኖቹ ጋር አያይዞ✍የፃፋቸው ዝርዝር የንድፈ-ሀሳብ ማብራሪያዎቹ ከብዙ መቶ #አመታት በኃላ ተግባራዊ ለሆኑ የፈጠራ ስራዎች መሰረት ጣይ ሆነዋል::ዳ ቪንቺ በዲዛይን ክህሎቱ በወረቀት ካሰፈራቸው ስራዎች ዋና #ዋናዎቹን እንመልከት:-

✈️#የበራሪ_ማሽን_ዲዛይን✈️

ዳ ቪንቺ ከብዙ የንድፈ-ሀሳብ የፈጠራ ስራዎቹ ውስጥ ትልቁ #ትኩረትን የሰጠው በአየር ላይ🛩ከመበረር ጋር የተያያዘ #ሃሳብን ነበር::ይኸው ዘመንን አሻግሮ ማየት የቻለ ምሁር የሰው ልጅ በአየር ላይ #እንዲበር ከፍተኛ💬ናፍቆት ነበረው:: ከሚታወቅባቸው የዲዛይን ስራዎቹ #በዋናነት ሊጠቀስ የሚችለው ከዚሁ ፍላጎቱ ጋር የተያያዘው "🔹#Flying_Machine🔹/🔸Orinithopter🔸" የሚባለው የበራሪ ማሽን ዲዛይኑ ነው::ምንም እንኳን የመጀመሪያው የተሳካ✈️የአውሮፕላን ፈጠራ እና በረራ የተከናወነው #በአሜሪካውያኑ👥ወንድማማቾች በ1903 ዓ.ም ቢሆንም ዳ ቪንቺ ከእነርሱ 400 ዓመታት በፊት ቀድሞ ባለራዕይ #አዕምሮውን በመጠቀምና የተፈጥሮ የበረራ ክህሎት ካላቸው🐧#አዕዋፋት ሃሳቡን በመውሰድ 33 ጫማ የክንፍ #ስፋት ያለውን የበራሪ ማሽን ዲዛይን #አድርጏል::

🚁#የሄሊኮፕተር_ዲዛይን🚁

ተግባራዊው #ሄሊኮፕተር በ1939 ዓ.ም ኢጎር ሲኮርስኪ በተሰኘ አሜሪካዊ-ሩሲያዊው የፈጠራ👤ባለሞያ #በአሜሪካ አገር የተፈጠረ ቢሆንም ዳ ቪንቺ ከ400 አመታት በፊት ዲዛይን ያደረገው "🔹#areal_screw🔹" የተሰኘው ባለራዕይ የፈጠራ ሃሳብ ዲዛይን #ለሄሊኮፕተር መፈጠር ፈር ቀዳጅ እንደሆነ ብዙዎች #ይገምታሉ::

#የፖራሹት_ዲዛይን

የፖራሹት #ፈጠራ በተግባር የዋለው #በፈረንሳዊው🚨የፈጠራ ባለሞያ ሉዊስ-ሰባስቲያን ለኖርማንድ በ1783 ዓ.ም ቢሆንም ዳ ቪንቺ ንድፈ-ሃሳቡን ከ300 ዓመታት በፊት🎯በባለራዕይነት #ክህሎቱ በዲዛይን🗒ማስታወሻው ላይ አስፍሮት ነበር::ከዚሁ ከፖራሹት ንድፉ ጋር አያይዞ✍በፃፈው ማስታወሻው ላይም "#ሰው_ድንኳን_በሚመስል_በተከፈተ_ትልቅና_ሶስት_መዓዘን_ቅርፅ_ባለው_የተወጠረ_ጨርቅ_ራሱን_አንጠልጥሎ⛰#ከከፍታ_ላይ_ራሱን_ቢወረውር_ያለምንም_ጉዳት_መሬት_ላይ_ማረፍ_ይችላል::" 🗣ብሎ ነበር::

#የታንክ_ዲዛይን

💎ይህ የዳቪንቺ ንድፈ-ሃሳብ በ1914 ዓ.ም በእንግሊዝ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለተፈጠረው #ዘመናዊ ታንክ ፅንሰ-ሃሳብን የሰጠ እንደሆነ🔭ይታመናል:: ዳ ቪንቺ በዚሁ ዲዛይኑ እንዳስቀመጠው ማሽኑ በሁሉም🎉#አቅጣጫ መሄድ የሚችል  #ጠላትን ለማጥቃት በሚያስችሉ በብዙ መሳራያዎች የተሞላ ሲሆን 360 ዲግሪ እየተሽከረከረ #መተኮስ የሚችልም አድርጎ ነበር ዲዛይን ያደረገው::


🎈ዳ ቪንቺ ከላይ ከተጠቀሱት ፈጠሪዎች በተጨማሪ🌅የፀሀይ ብርሀንን #እንደሀይል ምንጭ በመጠቀም የሚሰራ የመጀመሪያ ማሽን🕒ሰአት የሰውነት ክፍል ጥናት(human anatomy),የዋናተኛ #የውሀ ውስጥ መጥለቂያ መሳሪያ, #የጠብመንጃ,የውሀ ሃይል(hydrodynamics),የጠፈር  ምርምር, የኬሚካል ምህንድስና,የድልድይ,🎧የሙዚቃ መሳሪያ እና ሌሎችም በርካታ ድንቅ የፈጠራ ዲዛይኖችን #ያበረከተ👒ምሁር ነበር.:

🌂ሊዮናርዶ ከ1506-1510 ዓ.ም ባሉት ዓመታት ውስጥ የፃፈውንና #የፈጠራ ዲዛይኑን እንዲሁም የማብራሪያ ሃሳቡን ያሰፈረበት #ኮዴክስ_ሌስተር(Codex Leicester) የተሰኘው ባለ 61 ገፅ 🗒የማስታወሻ ደብተሩን አሜሪካዊው 💸ቢሊየነር  #ቢል_ጌትስ በ1994 ዓ.ም በጨረታ 💵በ30.8💵ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመግዛት #የግሉ አድርጎታል::ይህ ማስታወሻ ዳ ቪንቺ በህይወት ዘመኑ ከፃፋቸው ከ30 የሚበልጡ የሳይንሳዊ ፅሁፎችና ንድፎች #መካከል 💡አንዱ ነው::

#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

            🦋 SOT🦋
           

Post a Comment

0 Comments