የፈጠራ ስራ ሽመልስ ከአሰላ


ሽመልስ እባላለሁ የምኖረው ከአዲስ አበባ 175 km ርቀት ለይ በምትገኘው አሰላ ከተማ ነው ።
     በኑሮ ዝቅተኛ ከሚባሉ የህብረተሰብ ክፍል ነው እራሴን ያገኘሁት  ግን ልጅነቴን ሳስታውሰው በጣም እወደዋለሁ እግዚአብሔር ለኔ የሰጠኝ ልዩ ነገር እንዳለ ይሰማኛል  ሁለንም ነገር የጀመርኩት ከልጅነቴ ነው ።
   በትምህርት አገኘሁት የምለው ብዙ ነገር የለኝም ግን አዲስ ነገር መስራት እና የሆነ ቦታ ያየሁትን ነገር አስመስሎ መስራት እችላለሁ  የሆነ ነገር ለመስራት ካሰብኩኝ ሳላሳካው እንቅልፍ የለኝም ይሄ   የኔ ባህሪ ነው ።
      አሁን ከ አንድ አመት በፊት አንድ ሀሳብ በአእምሮየ ተመላለሰብኝ ለምን ሂሊኮፕተር አልሰራም የሚል እንቅልፍ አጣሁ ብዙ አሰብኩ  ለመስራትም ወሰንኩ ። እራሴንም አሳመንኩ ወደ ሳይንሱ እና ወደ ጥናቱ ገባሁኝ ኢንተርኔት ላይ ብዙ ነገር አየሁ ማስታወሻ ያዝኩ በሀሳቤ ዲዛይን አረኩ ።
     በመጨረሻም ስራውን ጀመርኩ  ሁሉም ነገር የተመቻቸ ባይሆንም ገባሁበት ያው ነገሮች ቀላል ይሆናሉ ብሎ መገመት አይቻልም መጀመርያ ቁርጠኝነት ያስፈልጋል ምክንያቱም የምሰራው ነገር ሚሞከረው እንቅስቃሴ ሚያደርገው  የመሬትን ስበት አሸንፎ  ከፍ ብሎ ስለሆነ በደንብ ማሰብ ይጠይቃል ።
    የግል ስራ ቢኖረኝም  ባለኝ  ጊዜ ለወራት ሰራሁት አንዳንዴ ከባድ ሁኔታዎች ያጋጥማሉ ነገሮች እንደታሰበው ላይሆኑ ይችላሉ   ያው በተስፋ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሷል  አሁንም ግን አላለቀም ሚቀሩኝ ነገሮች አሉ ሙከራውም ቢሆን እራሱን የቻለ ትልቅ ስራ ነው በሌሎች ሀገራት ሂሊኮፕተር ካለቀ በሀላ ሚሞከርበት የራሱ ማሽን አለው እዚህ ያ የለም ከዛ ከዛ አንፃር ነገሮች እንደታሰበው ላይሆኑ ይችላሉ ቢሆንም ግን ተስፋ አልቆረጥም  ።


#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

          🦋  SOT🦋
             




 

Post a Comment

0 Comments