በሰው በሚዘወር ፔዳል የሚበረው አውሮፕላን



በሰው በሚዘወር ፔዳል የሚበረው አውሮፕላን

በጃፓን የሚገኝ ካናዛዋ የተሰኘ ኢኒስቲቲዩት ከካርበን ልቀት ነጻ የሆነ በሰው ሃይል (በፔዳል) የሚንቀሳቀስ አውሮፕላን ሰርቶ የተሳካ ሙከራ አድርጓል፡፡

በሙከራ ደረጃ የሚገኘው አነስተኛ አውሮፕላን ÷ የሚበረው እንደተለመደው በሞተር ኃይል ሳይሆን በሰው በሚዘወር ፔዳል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡

የኢኒስቲቲዩቱ አጥኚዎች በሰው ኃይል የሚንቀሳቀሰውን አነስተኛ አውሮፕላን በጣም ቀላል ክብደት እንዲኖረው አድርገው ሰርተውታል።

ከዚህ ባለፈም አውሮፕላኑ ረዘም ያለ ርቀት እንዲበር ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

አውሮፕላኑን ለመስራት ፎም እንጨት እና ፕላስቲክ ጥቅም ላይ ውሏል መዋሉን የቴክኖሎጂ መረጃዎችን የሚያጋራው ቸየፎሲ ባይትስ መረጃ ያመላክታል።

#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

                 🦋  SOT 🦋
            

Post a Comment

0 Comments