በቻይና ሰው አልባ 5ጂ አየር ላይ ተንሳፋፊ ፊኛ የሙከራ በረራ አደረገ

 

በቻይና ሰው አልባ 5ጂ አየር ላይ ተንሳፋፊ ፊኛ የሙከራ በረራ አደረገ


በደቡብ ምዕራብ ቻይና ሰው አልባ አምስተኛ ትውልድ (5 ጂ) ኢንተርኔት የሚጠቀም አየር ላይ ተንሳፋፊ መርከብ የሙከራ በረራ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

 

ተንሳፋፊ መርከቡ ለወደፊት አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የመገናኛ አገልግሎት በመስጠት አስቸኳይ እርዳታ ለማዳረስ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

 

መርከቡ በዩናን ግዛት ከመሬት በላይ 300 ሜትር መብረር የቻለ ሲሆን ÷በቀጣይ በግዛቷ ለሚከሰተው የመሬት መንሸራተት፣ ጎርፍ እና ለሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል ለሚደረግ የእርዳታ ስራ እንደሚውል ታምኖበታል፡፡

 

የአየር ላይ መርከቡ ከ200 ኪሎ ግራም በላይ ጭነት በመሸከም 100 ካሬ ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ አገልግሎት መስጠት ይችላል ተብሏል፡፡

 

በአየር ላይ ከ15 ቀናት በላይ መንሳፈፍ የሚችለው ይህ መርከብ ÷ ኃይለኛ ንፋስን የመቋቋም ችሎታ እንዳለውም ተገልጿል፡፡


 #እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

                   🦋 SOT 🦋
              

Post a Comment

0 Comments