ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ ይጠየቃል


ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ሲያበር የተገኘ በሕግ ይጠየቃል - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

ስጋቶችን ለመከላከል ሲባል ድሮኖችን ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ ለቀረፃ መጠቀምም ሆነ ማብረር እንደማይቻል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሳሰበ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን በሀገሪቱ በሚካሄዱ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች ላይ ለቀረፃ ሲጠቀሙ እና ሲያበሩ እየተስተዋለ ነው ያለው አገልግሎት መስሪያቤቱ ጉዳዩ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከህገ ወጥ ድርጊታቸው ይቆጠቡ ሲል አሳስቧል።

ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ ድሮኖችን ለቀረፃ ሲጠቀም እና ሲያበር የተገኘ ማንኛውም አካል ወይም ግለሰብ በህግ እንደሚጠየቅ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስጠንቅቋል። (EBC)

via #tikvah

#እባኮትን ለጓደኛዎ #Share ያድርጉ‼️
         ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

                🦋  SOT 🦋
              

Post a Comment

0 Comments